በማኅበራዊ ድረ ገጽ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ 320 ሺህ ተከታዮችን አፍርቷል። Tana Award ጣና ሽልማት መጽሔት ላይ እንዲህ የሚል ታሪክ ተጽፏል፡፡
በማኅበራዊ ድረ ገጽ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ 320 ሺህ ተከታዮችን አፍርቷል። Tana Award ጣና ሽልማት መጽሔት ላይ እንዲህ የሚል ታሪክ ተጽፏል፡፡

በሁላችንም ኪስ ውስጥ የሚገኝ ሰው፣ ብርቧክስ የዓለም አጫዋች መንደር፣ ከሃያ ዓመታት ቀጠሮ በኋላ (በ9/9/99 ዓ.ም. 9 ሰዓት) የተቀጣጠሩ የጣና ሀይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች፣ የአርሆ መንገድ፣ ኾንሶ ኻኖ፣ የፀሐይ መዉጫ ልጆች፣ የጥበብ ገበሬ፣ የአርሲ ሳዱላ በመሳሰሉ ሥራዎቹ ሕዝብ ዘንድ አንቱታን አስገኝቶለታል።

በማኅበራዊ ድረ ገጽ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ 320 ሺህ ተከታዮችን አፍርቷል። Tana Award ጣና ሽልማት መጽሔት ላይ እንዲህ የሚል ታሪክ ተጽፏል፡፡

ጌጡ ተመስገን ውልደቱና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። በጋዜጠኝነት ሙያው፤ ለአገር እና ለሕዝብ በሠራቸው አይረሴ ሥራዎቹ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል።

የፈረንሳይ ቴሌቪዥን ባሰባሰበው የተመልካቾች ምዘና መሠረት “ባለንሥሩ ጋዜጠኛ ~ A Journalist with an eagle eye” የሚል ስያሜ አግኝቷል።

ሦስት ሥራዎቹም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ቀርበውለታል። በአዘጋጁቹ ግብዣ አውሮፓ ፤ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ቤልጅየም ትምህርታዊ ጉብኝት በማድረግ አገር ቤት ተመልሷል።

በ2002ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የመገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ የአረንጓዴ ሽልማት “በቴሌቪዥን ዘርፍ” አንደኛ ደረጃ ተሸላሚና የላቀ የክብር ዋንጫ ከቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ እጅ ተቀብሏል።

የኮንሶ መልክዓ ምድር የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ባደረገው ተከታታይ ሥራዎች በተለይ የጥበቃ ድንበር (Buffer zone) እንዲበጅላቸው ቀድሞ በቴሌቪዥን ዘገባው አገር እና ሕዝቡን በመቀስቀሱ ምክንያት ዩኔስኮ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንና የኮንሶ ልዩ ወረዳ በጋራ ሸልመውታል።

እኔ ለ12 ዓመታት አገር እና ሕዝብ በሙያዬ (እናንት ያገሬ ልጆች፤ የኢትዮጵያ ልጆች) ብዬ በትህትና ዝቅ ብዬ እያገለገልኩ ነበር። የዓመት እረፍት ላይ እያለሁ ነው መሰናበቴን የሰማሁት። ምክንያቱን በተመለከተ ድርጅቱን፤ እነርሱን ጠይቁ። በጣም ይቅርታ፤ ከድፍረት አትቁጠርብኝ እና በአክብሮት ስልክህን ልዘጋው ነው
እኔ ለ12 ዓመታት አገር እና ሕዝብ በሙያዬ (እናንት ያገሬ ልጆች፤ የኢትዮጵያ ልጆች) ብዬ በትህትና ዝቅ ብዬ እያገለገልኩ ነበር። የዓመት እረፍት ላይ እያለሁ ነው መሰናበቴን የሰማሁት። ምክንያቱን በተመለከተ ድርጅቱን፤ እነርሱን ጠይቁ። በጣም ይቅርታ፤ ከድፍረት አትቁጠርብኝ እና በአክብሮት ስልክህን ልዘጋው ነው

በቅርቡም በኢትዮ ሶሻል ሚዲያ አዋርድ በፈጣን፣ ተአማኒ ወቅታዊ መረጃ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

እንዲሁም በውቢቷ ባህርዳር በተካሄደው ጣና አዋርድ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2011ዓ.ም. የትምህርት ዘመን 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር) የሚገመት የነጻ ትምህርት እድል አበርክቶለታል።

ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ጋር በተደጋጋሚ በመደወል የስንብት ምክንያቱን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ” እኔ ለ12 ዓመታት አገር እና ሕዝብ በሙያዬ (እናንት ያገሬ ልጆች፤ የኢትዮጵያ ልጆች) ብዬ በትህትና ዝቅ ብዬ እያገለገልኩ ነበር። የዓመት እረፍት ላይ እያለሁ ነው መሰናበቴን የሰማሁት። ምክንያቱን በተመለከተ ድርጅቱን፤ እነርሱን ጠይቁ። በጣም ይቅርታ፤ ከድፍረት አትቁጠርብኝ እና በአክብሮት ስልክህን ልዘጋው ነው”

Source: news.et